ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀምሯል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከፍተኛ አመራሮች ክልል አቀፍ የዉይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)

መድረኩ ባለፉት የለዉጥ አመታት በብልጽግና ፓርቲ መሪነትና በህዝብ ተሳትፎ በተገኙ ድሎችና ባጋጠሙ ፈተናዎች ላይ የጋራ አረዳድና መግባባት በመፍጠር ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ መክፈቻ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ዉይይቱ የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት ሰሞኑን በአለምአቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ያሳለፈውን ዉሳኔ መነሻ ያደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በምክር ቤቱ ስብሰባ በመደመር መንገድ ወደ ብልጽግና በሚወስዱ መንገዶች ላይ በጥልቀት ዉይይት መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታዉሰዋል።

አለምአቀፋዊዉ እና ቀጠናዊዉ የፖለቲካ ሁኔታ ለሀገራችን ፈተናም፣ ዕድልም ይዞ መምጣቱን ጠቁመው በስክነት ዕድሉን መጠቀምና ፈተናዎችን በድል ለመሻገር መትጋት ይገባል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ በጊዜ ተገድበዉ የተቀመጡ ራዕዮች ማለትም በ 2018 ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሃን ከተቀመጠለት ጊዜ ቀድሞ መሳካቱ፣ 2023 የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌትና በ 2040 የዓለም የብልጽግና አርአያ የመሆን ዓላማን ለማሳከት መትጋት ከሁሉም እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

የብሔራዊ ራዕያችን መዳረሻ የሆነዉ ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ለትዉልድ ምንዳን ማዉረስ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑንም አስምረዋል።

በሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች መሪነትና አስተባባሪነት እንዲሁም በአንዳንድ ፅንፈኞች መሳሪያነት ለዉጡን ለመቀልበስና ኢትዮጵያን ለማሳነስ ዕኩይ ዓላማ አንግበዉ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን መመከት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በመድረኩ ከታሪካዊ ስብራትና ከአለምአቀፋዊና አከባቢያዊ ሁኔታዎች ተሞክሮ በመዉሰድ ብሔራዊ ጥቅምንና ተቋማዊ ጥንካሬን አጠናክሮ ለመዉጣት የሚያስችል አቅም ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።

መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት በተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር አመራሩን ለቀጣይ ተልዕኮ ማዘጋጀት ላይ ዓላማ ማድረጉም ተመላክቷል።

የምክር ቤቱ አቅጣጫን አስገንዝቦ ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ ማድረግ፣ በአመራሩ መካከል የዉስጥ አንድነትና የተግባር መቀራረብ መፍጠር፣ ክልሉን የሰላም፣ የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት በማድረግ በ 2018 የተቀመጡ ዕቅዶችን ማሳካት ከመድረኩ የሚጠበቁ ግቦች ናቸው።

ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት በሚካሄደው የዉይይት መድረክ የክልሉ መንግስት አስተባባሪ አካላትና አመራሮችን ጨምሮ የዞኖችና ሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች አስተባባሪ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *