አርባምንጭ፦ ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)
ከጋሞ ዞን ከሚገኙ መዋቅሮችና ከአርባ ምንጭ ከተማ የተወጣጡ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አመራሮችና አባላት “የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ የቤት ግንባታ አስጀምረዋል።
የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግባዬ ግልጮ ልዑካን ቡድኑ በጌዴኦ ዞንና ዲላ ከተማ አስተዳደር ያቀናው ከበጎ ስራ ባሻገር በሁለቱ ህዝቦች መካከል የቆየውን አብሮነት ለማስቀጠልና ሁለንተናዊ ወንድማማችነት ለማረጋጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የጌደኦ ዞን ወናጎ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሌ ሽፈራው በስፍራው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የጋሞና የጌደኦ ሕዝቦች የተቸገረን የመርዳት፣ የመጠየቅ ተፈጥሯዊ ችሮታ እንደተሰጣቸው አመላክተው ከጋሞ ዞንና ከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ተወጣጥተው የመጡ ልዑካንን አመስግነዋል።
ልዑካን ቡድኑ በዲላ ዩኒቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ጊቢ በመገኘት ታካሚዎችን በመጠየቅ በሆስፒታሉ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችንና የመስህብ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።
በጌደኦ ዞን ወናጎ ወረደ ጀምጀሞ ቀበሌ የተገኙት የልዑካን አባላት ስድስት ልጆችን ብቻዋን ለሚታሳድገው አቅመ ደካማ እናት ቤት መገንቢያ የሚሆን ቆርቆሮ፣ ሚስማርና የቤት ቁሳቁስ አበርክተዋል።
በስፍራው የጋሞ ዞን፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር፣ የጌዲኦ ዞን ወጣቶች ክንፍ አመራሮች፣ የወናጎ ወረዳ የመንግስትና የፓርቲ የስራ ኃላፊዎችና የቀበሌ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።