አርባ ምንጭ፤ ነሐሴ 07 /2017 ዓ.ም. (ጋሞ ቴሌቪዥን)
የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የህብረተሰቡ የኑሮ እንዲቃለል አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን በጋሞ ዞን የካምባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ገለፀ።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ መለሰ ለጋሞ ቴሌቪዥን እንዳሉት በከተማው ወጣቶች በልማት ሥራዎች የሚያደረገት ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።
ወጣቶቹ በተለይም ለበርካታ አቅመ ደካማ ወገኖች ቤት በመገንባት እና ሌሎች በጎ ተግባራትን ማከናወናቸውን ገልጸዋል።
በጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማው ባህል እየሆነ መጥቷል ያሉት ኃላፊው ይህም የህብረተሰቡን ኑሮ እያቃለለ ነው ብለዋል።
አቅመ ደካማ እና በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት የካምባ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አማረች ሰጻና ያረጀ ቤታቸው በክረምት ለዝናብ በበጋ ደግሞ ለፀሐይ ሲያጋለጣቸው እንደነበር ያስታውሳሉ።
በበጎ ፈቃድ የተገነባው አዲሱ መኖሪያ ቤታቸው ይህን ችግር እንደፈታላቸው ገልፀዋል።
አቶ ዱንቻ ዱሮ በበኩላቸው ወጣቶች እያከናወኑ በሚገኙት በጎ ተግባር መደሰታቸውን ይናገራሉ።
የካምባ ከተማ ወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ወጣት ዮሴፍ ዮንግረና ወጣቶች በከተማው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ችግሮች እየተፈቱ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ፕሬዚዳንቱ ያመለክታሉ።