የጥምቀት በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

የጥምቀት በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

አርባ ምንጭ፦ጥር 11|2017 ዓ|ም (ጋሞ ቴቪ)፦

የጥምቀት በዓል በአርባ ምንጭ በከተማ በፈለገ ዮርዳኖስ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ብፁዕ ወቅዱስ ሊቀጳጳስ አቡነ ኤሊያስ እና ብፁዓን አባቶች ተገኝተዋል።

በዓሉ ክቡር ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የቤተ ክህነት ኃላፊዎች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንትና ካህናትና በርካታ ምእመናንና የውጭ ሀገራት ዜጎች በተገኙበት በአርባምንጭ ሲቀላና ሴቻ ፈለገ ዮርዳኖስ እየተከበረ ይገኛል።

ባሕረ ጥምቀት ከንጋቱ ጀምሮ ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች የተካሄዱ ሲሆን፤ በብፁአን አባቶች የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዶ ቅዱሱን ፀበል ለምዕመናን እያዳረሱ ይገኛል።

በዓሉ የቃል ኪዳኑ ተምሳሌት የሆኑ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው በመመለስ በድምቀት ተከብሮ ይውላልም።

በተጨማሪም ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *