የጋሞ የቴሌቪዥን ጠንካራ የአደረጃጀትና የአስራር ስርዓት የቴሌቪዥን ጣቢያው በአጭር ጊዜ ልምድ የሚቀሰምበት ጣቢያ እንዲሆን ማስቻሉን የሀዲያ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ አቡሌ ገለፁ።

የጋሞ የቴሌቪዥን ጠንካራ የአደረጃጀትና የአስራር ስርዓት የቴሌቪዥን ጣቢያው በአጭር ጊዜ ልምድ የሚቀሰምበት ጣቢያ እንዲሆን ማስቻሉን የሀዲያ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ አቡሌ ገለፁ።

በሀዲያ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ አቡሌ የተመራ ልዑክ የጋሞ ቴሌቪዥን ጣቢያ የስራ እንቅስቃሴ በመጎበኘት ልምድ ልውውጥ አድርጓል።

አርባምንጭ፥ ጥር 9/2017 ዓ/ም(ጋሞ ቴሌቪዥን)፦

የሀዲያ ቴሌቪዥን አመራር ልዑኩን የመሩት የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ስራ አስፋፃሚ አቶ ወንድሙ አቡሌ የጋሞ ቴሌቪዥን የተቀናጅ አደረጃጀትና አስራር ስርዓት የቴሌቪዥን ጣቢያው በአጭር ጊዜ ፈጣን ለውጥ እንዲያመጣ አስችሏል ብለዋል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው የይዘት ስራ እና የቴክኖሎጂ አደረጃጀትና አጠቃቀም በተመለከተ ግንባር ቀደም እየሆነ እንደሚገኝ አንስተው፤ ከጣቢያው መልካም ተሞክሮ ልምድ መቅሰም መቻላቸውን አስርድተዋል።

በጋሞ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተመለከቱትን ጠንካራ አደረጃጀት፣ አሰራርና የስራ ባህልን ይበልጥ ማጎልበት በሀዲያ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እንደሚረዳም አክለዋል።

የሁለቱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙርያ በአብሮነት ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈፃማቸውንም ገልፀዋል።

የጋሞ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አዲሱ አዳሙ ቴሌቪዥን ጣቢያውን የፕሮግራምና ዜና አቀራረብ፣ የይዘት አዘገጃጀትና የተቋማዊ አደረጃጀትን በተመለከተ ለሀድያ ቴሌቭዥን ልምድ ማጋራት እንደተቻለ ገልፅዋል።

በቀጣይ ሁሉቱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች መረጃዎችን በመጋራት የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከርና በአብሮነት ለመስራት መስማማታቸውን አስገንዝበዋል።

በየደረጃው በሚገኘው አመራርና ማህበረሰቡ ጠንካራ ድጋፍ ቅርብ ጊዜ መደበኛ ስርጭት ጀምሮ በአጭር ጊዜ አበረታች ለውጥ ያመጣ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ መሆን መቻሉንም አስገንዝበዋል።

በቴሌቪዥን ጣቢያው ፈጣን ለውጥ የተነሳ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የተሻለ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ በማለት እውቅና የሰጠ መሆኑን አውስተው፤ ጠንካራ ጎንን በይበልጥ በማጠናከርና ክፍተቶችን በማሻሻል በሀገር ደረጃ ካሉ ምርጥ የሚዲያ ተቋማት አንዱ ለመሆን በአፅንኦት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

የሀዲያ ቴሌቪዥን ሚዲያ ተክኖሎጂ ዲቪዥን ኃላፊ አቶ አዲስዓለም ብርቀ ከልምድ ልውውጡ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠራቸውን ተናግረዋል።

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *