“ስፖርት ለማህበራዊ ትስስርን እና ለህብረብሔራዊነት የጎላ ሚና አለው።”አቶ አለማየሁ ባውዲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ

አርባምንጭ ጥር 13/2017(ጋሞ ቴቪ)

የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ልማት ፕሮግራም የምዘና ውድድር የጋሞ ዞን እግርኳስ ፕሮጀክት ከወላይታ ዞን አቻው ጋር በሚያደርገው የመክፈቻ ጨዋታ ተጀምሯል።

በመረሃ ግብሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ ስፖርት ለማህበራዊ ትስስር እና ለህብረብሔራዊ አንድነት የጎላ ሚና አለው ብለዋል።

ለአመታት ተቋርጦ የነበረው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ልማት ፕሮግራም የምዘና ውድድር ዳግም መጀመሩ ታዳጊዎች በስፖርቱ ዘርፍ ውጤታማ ሆነው ሀገርን እንዲወክሉ ያስችላል ብለው ፡፡

የውድድሩ ተሳታፊዎች በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲፎካከሩ ገልፀው ያላቸውን ክህሎት በመጠቀም ክልሉን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለማድረግ እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

ክህሎት ያላቸው ታደጊዎች በአካዳሚዎች እንዲካተቱ እና በክለቦች እንዲታቀፉ መንገድ የሚከፍት መሆኑን የጠቆሙት አቶ አለማየሁ ለሀገር አቀፍ ውድድር ክህሎት ያለቸውን ስፖርተኞች በፍትሀዊነት መመልመል ላይ በትኩረት እንዲሰራም አስገንዝበዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኦላዶ ኦሎ በበኩላቸው ስፖርት ወዳጅነት የማጠናከር አቅም ያለው የልማት መሳርያ በመሆኑን በቀጣይም በሁሉም ደረጃ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

የወላይታ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ ተመስገን ታደሰ በስፖርቱ ዘርፍ ስኬታማ መሆን የሚቻለው በትጋት በመስራት መሆኑን ገልጸው ታዳጊዎች ውጤታማ ለመሆን ጠንክረው መስራት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ የክልሉ፣የዞኖች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ተወዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት መክፈቻ መርሃ-ግብሩ ተገኝተዋል

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *